
ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ አንድ ሀገር ሳትሆን በወሮ በላ ተከፋፍላ በክልል ታጥራ እንድትኖር በህወአት ማኒፌስቶ(ሕገመንግስት) ፅሑፍ ተረቆላት፣ ህዝቦቹ በፊት ያልነበሩ፣ እንደአዲስ ተፈጥረው ለመሬት፣ ለወደብ፣ ለዳርድንበር፣ ለቋንቋ፣ ለባሕልና ለታሪክ፣ ለአንድነትና አብሮ መኖር እሴት ላይናገሩ እንኳንም በቁማቸው ስለሚኖሩበት መሬትና መብት ፣ሞተውም ኪራይ የሚከፍሉባት የመጤዎች መስፈሪያ ስትባል ህዝቡ ፣ባርኔጣውን ደፍቶ፣አንገቱን በሻርብ አስሮ፣ በቀን በቀን ዘፈን እየነገደ እንደከብት ሲፈነጥዝ 22 ኣመት አለፈ።