
ሁለቱ የቻይና ኩባንያዎች ሁዋዌና ዜድቲኢ ለሚያከናወኑት የ1.6 ቢሊዮን ዶላር የሞባይል ኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አማካሪ ድርጅት ለመቅጠር ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቷል፡፡
ጨረታውን ያወጣው የፕሮጀክቱ ባለቤት ኢትዮ ቴሌኮም ነው፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ አማካሪ ድርጅቱን ለመቅጠር የወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም. በይፋ ይከፈታል፡፡