በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ የሞራል ኪሳራ፣
ኢትዮጵያውያን/ት ለዓለም ባንክ የጭካኔ ቢሮክራሲያዊ የቀልድ ማካሄጃ የመድረክ ትወና ዒላማነት ተዳርገዋል፡፡
በምዕራብ ኢትዮጵያ ጋምቤላ እየተባለ በሚጠራው ክልል የዓለም ባንክ ቢሮክራቶች ዜጎችን ከሰፈሩበት ቦታ ያለፈቃዳቸውወደ ሌላ ቦታ በማዛወር፣የአካባቢው ዜጎች በቋሚነት ባህላቸውን አዳብረው ከሚኖሩበት ቦታቸው በግዳጅ በማፈናቀል እናየተለሳለሰና እና በጎ መስሎ በእሬት የተለወሰ የዘርማጽዳት እኩይ ምግባር በማካሄድ “የማታለል ጨዋታ” በመጫወት ላይመሆኑን አንድ ያለም ባንክ የራሱ የምርመራ ዘገባ ባለፈው ሳምንት ይፋአድርጓል፡፡