የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደትን አስመልክቶ ሁለተኛ ዙር ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የወያኔ/ኢህድግን ስርአት አስወግዶ በሁሉ አቀፍ የሽግግር መንግስት የመተካትን
ሂደት አስመልክቶ ሁለተኛ ዙር የምክክር ጉባኤ በማዘጋጀት ሂደት ላይ መሆኑን መግለድ ይወዳል።
የሽግግር ምክር ቤቱ ባለፈው ጁላይ ወር 2013 የተለያዩ ተወካዮች፤ ከፖለቲካ ድርጅቶች፤ ከሲቪክ ማህበራት፤ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ፤ ከሃይማኖት ተቋማት፤ ከታዋቂ ምሁራንና ከመገናኛ ብዙሃን የተሳተፉበት ታሪካዊ የምክክር ጉባኤ አካሂዶ የሽግግር ቅድመ ዝግጅት ሂደት እንዲጠናከር የሚያግዝ ኮሚቴ መቋቋሙ የሚታወስ ነው።