Wednesday, January 22, 2014

በቦረና ኦሮሞና በቡርጂዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሰዎች እየተሰደዱ ነው

ቦረና አከባቢ የሚኖሩ ቡርጂዎች እየተሰደዱ ነው፡፡ ከአከባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የግጭቱ መንስኤ በቡርጂ መንደር ተገድሎ ተገኘ ተባለ የቦረና ብሄረሰብ አባል አስከሬን ነው፡፡

አንቶኖቭ 28 አውሮፕላን በለገዳዲ አካባቢ ተከሰከሰ



ንብረትነቱ የዩክሬን የሆነ አንቶኖቭ 28 የመንገደኞች አውሮፕላን ከኡጋንዳ ኢንቴቤ ተነስቶ ወደ ሰንዓ የመን በመብረር ላይ እንዳለ ባለፈው ሰኞ አዲስ አበባ አቅራቢያ ለገዳዲ አካባቢ መከስከሱን ሪፖርተር ጋዜጣ ከአዲስ አበባ ዘገበ። ጋዜጣው ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አገኘሁት ባለው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ የአውሮፕላኑ አብራሪዎች ሰኞ ማለዳ ከባለሥልጣኑ ጋር ባደረጉት የሬዲዮ ግንኙነት ከኢንቴቤ ተነስተው በኢትዮጵያ በኩል ወደ የመን ለመብረር ፈቃድ ጠይቀው ነበር፡፡ ባለሥልጣኑም የበረራ ፈቃድ ሰጥቷቸዋል፡፡

የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ

የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ‹መዝገበ ቃላት› ለነፃነት የሚሰጠው ትርጓሜ ‹አራምደዋለሁ› ከሚለው ግራ-ዘመሙ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ብያኔ አንፃር የሚተነተን በመሆኑ፣ የየትኛውም ተቋም ነፃ ሆኖ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ረዣዥም እጆቹን ደጋግሞ እየጫነ ሲጨፈልቅና ሲያስጨፈልቅ ለመኖሩ በርካታ ማሳዎችን ማቅረብ ይቻላል።

Monday, January 20, 2014

“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል” ቴዲ አፍሮ



በሳምንቱ መጨረሻ ቴዲ አፍሮ ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ነበረው፡፡ በሁለት ክፍል የተደረገውን ቃለ-ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል እነሆ ፡)

Prof. Mesfin Woldemariam

በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ

በሃይማኖት ጭቆና ስም የሚረጩ አደገኛ መርዞች

አራተኛውን የኢቲቪ “ጥናታዊ ፊልም” አየሁት፤ ዝቅ ሲል ለምርጫ ቅስቀሳ፣ ከፍ ሲል ደግሞ ከፋፍሎ ለመግዛት ተብሎ የተዘጋጀ ይመስለኛል። ፊልሙ ኢህአዴግንና የቀድሞ ስርዓቶችን ያነጻጽራል፤ ማንም ነፍስ ያለው ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ጭቆና አልነበረም ብሎ አይክድም፤ ልዩነቱ የሚጀመረው “ጨቋኙ ማን ነው? ተጨቋኙስ?” የሚለውን ለመመለስ ሲሞከር ነው።

የአውራው ፓርቲ “ብዥታዎች” በዝተዋል!

የኒዮሊበራሊዝም ኃይሎች በአሸባሪነት ተፈርጀዋል እንዴ?
የኢኮኖሚ ዕድገቱን መካድ “ከሃዲነት” ነው!
“የመንግስት ሚዲያዎች በባህርያቸው የአውራው ፓርቲ ልሳን ሆነዋል”
<እውነቱን ለመናገር በአሁኑ ወቅት “ማጥራት” የሚፈልጉ “ብዥታዎች” እንደ ጉድ ተበራክተዋል (የቃላቱ ኮፒራይት የኢህአዴግ መሆኑ ልብ ይባልልኝ!) እናላችሁ ….. የዛሬ ፖለቲካዊ ወጌ በእነዚህ “ብዥታዎች” ዙርያ ያጠነጥናል፡፡