በባህር ዳር የአንድ እንግሊዛዊን ድንገተኛ ሞት እየመረመርኩ ነው ያለው ወያኔ/ኢህአዲግ ”በታህሳስ 9/2007 ዓም የአምስት ሰዎችን ሞት እና የአንድ መነኮሳይትን ጨምሮ የሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ደም መፍሰስ ትክክል ነበር” የሚል ሰልፍ እያዘጋጀ ነው.
ወንበዴ መሪ በሆነበት ሀገር ፍትህ መቀለጃ ትሆናለች።ሕግ፣ስርዓት እና ምክንያታዊነትን ዜጎች ቢናፍቁም ህገወጦች ስልጣን ከተቆናጠጡ ዙርያቸውን በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶም ጭምር የሚኮለኩሏቸው ለሆዳቸው እና ለጥቅማቸው ብቻ የሚሰለፉቱን ነውና ብዙ ጆሮ የሚጠልዙ ነገሮችን መስማት ይለመዳል።