የሽግግር መንግስት ምስረታ ሂደትን አስመልክቶ ሁለተኛ ዙር ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባኤ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት የወያኔ/ኢህድግን ስርአት አስወግዶ በሁሉ አቀፍ የሽግግር መንግስት የመተካትን
ሂደት አስመልክቶ ሁለተኛ ዙር የምክክር ጉባኤ በማዘጋጀት ሂደት ላይ መሆኑን መግለድ ይወዳል።
የሽግግር ምክር ቤቱ ባለፈው ጁላይ ወር 2013 የተለያዩ ተወካዮች፤ ከፖለቲካ ድርጅቶች፤ ከሲቪክ ማህበራት፤ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ፤ ከሃይማኖት ተቋማት፤ ከታዋቂ ምሁራንና ከመገናኛ ብዙሃን የተሳተፉበት ታሪካዊ የምክክር ጉባኤ አካሂዶ የሽግግር ቅድመ ዝግጅት ሂደት እንዲጠናከር የሚያግዝ ኮሚቴ መቋቋሙ የሚታወስ ነው።
ከስርአቱ ውድቀት በኋላ ስርአቱን የሚተካ ሃይል ላይ ምክክር በማድረግ የጋራ ስምምነት ላይ ባልተደረሰበትና ቅድመ
ዝግጅት፤ ባልተደርገበት ሽግግር፤ ሃገራችን ኢትዮጵያ አሁን በግብጽና በሌሎች የአለም ሀገራት ከምናየው የከፋ ችግር
ውስጥ እንዳትገባና ህዝቧም ለከፈተኛ አደጋና ቀውስ እንዳይጋለጥ፤ የሂደቱ መጀመርና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ የሽግግር
ምክር ቤቱ ዋንኛ አላማ ነው።
ዝግጅት፤ ባልተደርገበት ሽግግር፤ ሃገራችን ኢትዮጵያ አሁን በግብጽና በሌሎች የአለም ሀገራት ከምናየው የከፋ ችግር
ውስጥ እንዳትገባና ህዝቧም ለከፈተኛ አደጋና ቀውስ እንዳይጋለጥ፤ የሂደቱ መጀመርና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ የሽግግር
ምክር ቤቱ ዋንኛ አላማ ነው።
የሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ፤ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎች አሰላለፍ፤ ጂኦ ፖለቲካውንና የውጭ ሃይሎች ፍላጎት ሲታይ
የያዝንው አላማ መሪ አጀንዳ ሆኖ የሚወጣበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ መድረሳችንን ከመቼውም የበለጠ ተገንዝበናል።
በመሆኑም በጁላይ ወር ከተካሄደው የምክክር ጉባኤ የሰፋና ተጨማሪ ተወካዮችን (stakeholders) ያሳተፈ የሁለተኛ ዙር የምክክር ጉባኤ ለማዘጋጀት የሽግግር ምክር ቤቱ ጠንክሮ በመስራት ላይ መሆኑን መግለድ እንወዳለን።

ሁላተኛው ዙር የምክከር ጉባኤ የሚደረግበትን ቦታና ቀን እንዲሁም ተያያዥ ዝርርዝር ጉዳዮችን አስመልክቶ
ማብራሪያዎችና መግለጫዎች ወደፊት እንደሚሰጡ እናሳውቃለን።
ማብራሪያዎችና መግለጫዎች ወደፊት እንደሚሰጡ እናሳውቃለን።
ለዘላቂና አስተማማኝ ለውጥ ሁሉን አቀፍ ምክክር ማድረግ ወቅታዊ ነው!
No comments:
Post a Comment