**ONE NATION,ONE COUNTRY,ONE ETHIOPIA,ONE FLAG** ***FREEDOM FOR ETHIOPIANS AND ELIMINATION FOR EPRDF/TPLF***
Saturday, April 27, 2013
Another big lies from Ethiopian Embassy Stockholm - new press release
በኖርዌይ ስታቫንገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ትውልደ
ኢትዮጵያውያን ቦንድ በመግዛት ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን
ቁርጠኝነት አረጋገጡ
በኖርዌይ አገር ስታቫንገር ከተማ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ሽፋኖች
የተሰባሰቡ ፀረ-ሰላምና ልማት ሀይሎች ያቀነባበሩት የጥገኝነት ጠያቂዎች የተቃዉሞ ሰልፍ ሳይገድባቸው ለህዳሴ ግድብ
ግንባታ የሚውል የ75 ሺህ የኖረዌይ ክሮነር (250,000 ብር) የሚያወጣ ቦንድ በመግዛት ለአገራችን ልማት ያላቸውን
ቁርጠኝነት በተግባር አስመሰከሩ።
በስዊድን ስቶክሆልም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆ/ጄ/ፅ/ቤት በስታቫንገር ከሚገኙ በፈቃደኝነት ከተሰባሰበቡ ኮሚኒቲ አባላት ጋር
በመተባበር April 20, 2013 የውይይት መድረክ በማዘጋጀት ኢትዮጵያዉያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን መጋበዙ
ይታወቃል። የስብሰባው ዓላማ የህዳሴ ግድብ ቦንድ መሸጥና ቆ/ጄ/ፅ/ቤቱ በሚሰጠው የአገልግሎት ዙሪያ ላይ ገለፃ
መስጠት ነበር። የተለያዩ ፀረ-ልማት ሀይሎች የጥገኝነት ጥያቄ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን በማሰባሰብ ፖሊስ ቶሎ
ያለመድረሱን ክፍተት ተጠቅመው ወደ ስብሰባ ቦታው በመግባት ረብሻ ፈጥረው ስብሰባው ለጊዜው ቢቋረጥም፤ አገር
ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያዉያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያዘጋጀነው የህዳሴ ግድብ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በፀረ-
ልማት ሀይሎች እኩይ ተግባር ምክንያት አይገታም በማለት በአጭር ጊዜ እርስበርሳቸው በተለያየ መልኩ ግንኙነት
በመፍጠር ስብሰባው በሌላ ቦታ እንዲቀጥል በማድረግ ለአገራቸው ልማት ያላቸውን ድጋፍ ቦንድ በመግዛት
አረጋግጠዋል።
በዘህ አጋጣሚ ሰልፈኞቹ ወደ አዳራሽ እንዴት ገቡ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ስለሚችል በአጭሩ መግለፁ ተገቢ ይሆናል።
ኦነግ ነኝ የሚል ቡድን በወሰደው ፈቃድ መሰረት ከ1-4pm ባለው ጊዜ ውስጥ ሰልፍ ለማድረግ የተፈቀደለት ሲሆን
የሚስዮኑ ስብሰባ ግን 3pm ላይ የሚጀመር ነበር። የሚስዮኑ አባላት ስብሰባውን ለመጀመር ከጥቂት ታዳሚዎች ጋር
ልክ በተቀመጠላቸው ሰዓት ወደ አዳራሹ መግባት ሲጀምሩ በአካባቢው ፖሊስ አለመኖሩን ያረጋገጡ ሰልፈኞች
ከተከለላቸው ቦታ በማለፍ ወደ አዳራሹ በመግባት ብጥብጥ ጀመሩ፤ ፖሊስም ቆይቶ ደረሰ። አዳራሹ ትንሽ ስለነበረና
በዋናነት በሚረብሹትን በመያዙ ተሰብሳቢውን ለማስገባት ሰለማይበቃ የሚስዮን ተወካዮች ፖሊስን ስብሰባው
እንዲቋረጥ እንዲያደርግ ጠየቁ። በዚህም መሰረት ፖሊስ የዲፕሎማቶቹ ደህንነት የማስጠበቅ ግዴታ ስላለበት
ዲፕሎማቶችን አስወጥቶ ወደ መኪናቸው ካስገባ በኋላ የነበረው ለጥገኝነት ጥያቄ ለማስረጃነት ይረዳ ዘንድ ፎቶ
የመነሳትና የመጮህ ድራማ በዚሁ ያበቃ ሲሆን የሚስዮኑ ዓላማ ግን በዚህ እኩይ ተግባር ሳይሰተጓጎል በሚገባ መልኩ
ማሳካት ተችሏል። የኖርዌይ ፖሊስም ለምን እንደዘገየ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ለሰልፈኞቹ ቦታና ጊዜ ወስኖ ሰጥቶ
ስለነበረ እንደዚህ አይነት ጥሰት ይፈፀማል ብሎ ባለመገመቱ የተነሳ መሆኑን ገልጿል።
ቆ/ጄ/ፅ/ቤቱ የአገራችን ልማት ለግል ጥቅም አገርን ማተራመስ በሚመኙ ሀይሎች ምክንያት ለአንዲት ሰከንድ እንኳን
እንደማይገታና በኖርዌይ ከዚህ በኋላም በርካታ ፕሮግራሞችን እንደሚያካሂድ ለመግለጽ ይወዳል። አገር ወዳድ የሆኑ
ኢትዮጵያዉያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለአገራችን ልማት እያደረጉት ያለው ድጋፍ በይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል
ጥሪዉን ያስተላልፋል። በዚሁ አጋጣሚ ይህን መድረክ ያዘጋጀው ኮሚቴም የተቻለውን ዝግጅት በማድረጉና ሌላው
ተሳታፊም በመደናገጥ ሳይበተን የመሰብሰቢያ ቦታ በመቀየር ድጋፉን በሚያረካ መልኩ በመፈፀሙ የላቀ ምስጋናችንን
እናቀርባለን።
የኢትዮጵያ ልማት ተጠናክሮ ይቀጥላል፣
ታላቁ የህዳሴ ግድብም በህዝባችን ተሳትፎ እዉን ይሆናል!
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆ/ጄ/ፅ/ቤት
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment