Friday, October 24, 2014

ጄነራል ኃይሉ ጎንፋ ያሉበት የኦነግ ከፍተኛ አመራር ጄነራል ከማል ገልቹን ከስልጣን ማንሳቱን አስታወቀ

http://www.zehabesha.com/amharic/wp-content/uploads/2012/04/kemal_gelchi-1-1.jpg

(ዘ-ሐበሻ) በአስመራ የሚገኘውና በጀነራል ከማል ገልቹ ይመራ የነበረው ኦነግ መሪውን ከስልጣን ማንሳቱን ዘ-ሐበሻን ጨምሮ በተለያዩ ሚዲያዎች በበተነው መግለጫ አስታወቀ።

በዶ/ር ኑሮ ደደፎ፣ በምክትላቸው ብርጋዴር ጄነራል ሃይሉ ጎንፋና በአቶ ዳባ ጉተማ በኩል የበለጠ መረጃ ታገኛላችሁ በሚል የኦነግ ከፍተኛ አመራር ባወጣው መግለጫ ብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ ከስልጣን እንዲነሱ የተደረገበትን ምክንያት አብራርቷል። ዘ-ሐበሻ መግለጫውን ኦነግ የሕግ ጉዳዮችና የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ ከዶ/ር ኑሮ ደደፎ ለማረጋገጥም ችላለች።
በሌላ በኩል ከስልጣን ተነሱ የተባሉት ጀነራል ከማል ገልቹም እንዲሁ በበኩላቸው መግለጫ ሊሰጡ ይችላሉ እየተባለ ሲሆን ዘ-ሐበሻ እርሳቸውን ለማግኘት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም።

No comments: