
ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት፡- ባለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የሚዲያ ነጻነት እንደሚፈቀድ ቢደነግግም በተግባር ግን የራሱን ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛባቸው ሚዲያዎች ውጭ ሌሎቹን ሲዘጋና ሲያሸማቅቅ ኖሯል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ህዝባችን ከገዥው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ውጭ አማራጭ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ፣ እየተሰደዱ፣ ሚዲያዎች እየተዘጉም ቢሆን የተቻላችሁን ያህል ለህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ለምታደርጉት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር አለን፡፡ የታፈነውን የህዝብ ድምጽ ለማሰማት የምታደርጉትን ጥረትም እናበረታታለን፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በገዥው ፓርቲ አፋኝነት ምክንያት ህዝባችን የሚገባውን መረጃ እያገኘ አይደለም፡፡ እናንተም በሰበብ አስባቡ ጫና እየደረሰባችሁ እንደሆነ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡
No comments:
Post a Comment