
የማዕከላዊ ሃላፊዎች ግን ለምን ዝም ይላሉ
በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈጸም በየጊዜው የሚወጡ ሪፖርቶች ከማጋለጣቸውም በላይ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ዜጎች በምርመራ ላይ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው በመጥቀስ አንዳንዶቹ ልብሳቸውን እያወለቁ ጭምር ሲያሳዩ ማስተዋላችን አልቀረም፡፡
ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች መካከል በተለይ የቀድሞው የሸሪዓ ፍርድቤት ፕሬዝደንት ሼኽ መከተ ሙሄ በማዕከላዊ ፊደል የማይገልጸውን የመብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈጸም በየጊዜው የሚወጡ ሪፖርቶች ከማጋለጣቸውም በላይ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ዜጎች በምርመራ ላይ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እንደተፈጸመባቸው በመጥቀስ አንዳንዶቹ ልብሳቸውን እያወለቁ ጭምር ሲያሳዩ ማስተዋላችን አልቀረም፡፡
እኔ የምለው
ፍርድ ቤቱ እንዲህ አይነት አሰቃቂ ወንጀል በምርመራ ስም ዜጎች ሲናገሩ እያደመጠ‹‹ሁለተኛ እንዳይደገም››በሚል ቃል የሚያልፈው እስከመቼ ነው?ተሰቃየን ቶርቸር ተፈጸመብን ያሉ ተጠርጣሪዎችን የዋስ መብት ነፍጎ በወህኒ እንዲቆዩ ማድረግስ መልሶ ለገራፊዎቻቸው አሳልፎ መስጠት አይሆንምን?
የማዕከላዊ ዝምታ
የስቃይ ቤት ስለመሆኑ እየተነገረለት የሚገኘው ማዕከላዊ ስለሚቀርቡበት ሪፖርቶችና ማስረጃዎች ስለ ምን ዝምታን መረጠ?እንዲህ ያደረጉ ፖሊሶች እንደሌሉት ወይም ጨለማ ክፍል ፣ቀዝቃዛ ቤት መግረፊያ ክፍል እንደሌለው ለምን ህዝብ እንዲጎበኘው አያደርግም፡፡እግረ መንገዴንም ማዕከላዊ ለህዝብ ክፍት ይሁን የሚል ጥያቄዬን ላቅርብ፡፡
No comments:
Post a Comment