Sunday, October 27, 2013

ወንጀል – ከደደቢት አስከ አራት ኪሎ

75f9c-64714_277529845721314_403137022_n
ፈሪ በጩኸት ብቻ በርግጐ የመቃብሩን ግዜ ያፋጥናል ይኽንንም ከጨካኙ መሪያቸው ሞት በቀላሉ ለመረዳት ችያለሁ።
አሁንም  የሚታየው እውነት እንደሚያሳየው አዲስ አበባ ወጥተው የሚጮሁትን ፈርተው እየደጋገሙ የፍርሓት ዛቻ ሲያዘንቡባቸው ይሰማሉ፤ አንዳንዶችንም ይመታሉ ፣ያስራሉ፣ የሚፈልጉትን ሁሉ ያደርጉባቸዋል። ከዚህ ድርጊታቸው ስንነሳ አሁን እየፈጸሙ ያሉት ድርጊት ቀድሞውንም ሲፈጽሙት የነበረና አሁንም ያለቀቃቸው መሆኑን ስመለከት ህወሓቶች ኢትዮጵያዊ ስነምግባርና አስተዳደግ የጐደላቸው ፣ በክፋታዊ አስተሳሰባቸው የተበረዙ፤ የሌሎች ጭቁን ህዝቦችን ህልውና እየተዳፈሩ እነሱ ብቻ ነፃ አውጭ እነሱ ብሎ ነፃ አውጭ፤ ሌላው ለራሱ ነፃ መውጣት የማይታገልና እነሱ ባዘጋጁት የክፋት መዋቅር ውስጥ ለሁሌም እየገዙት የሚኖሩ የሚመስላቸው፤ እነሱ ለዚህ ክፋታዊ ግባቸው እንደታገሉ ሁሉ ለእውነተኛው ነጻነትማ ህዝቡ ለምን አይታገላቸው? ህወሓቶች እጅግ በታሪክም፣ በሰውምና በአምላክም ፊት የ39 አመታትየወጀለኝነት ዶሴዎች ጥርቅም በፊታቸው ያለ መሆናቸውን የተረዳሁበት እጅግ መራራ ጽሁፍ ነበር ያነበብኩት ።

No comments: