Wednesday, January 29, 2014

የሀሮማያው ዩኒቨርስቲው ብጥብጥ ዝርዝር መረጃ



በሀሮማያ ዩኒቨርስቲ የቴክኖሎጂ ተማሪዎች የሚማሩበት ገንደጄ የተባለው ግቢ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ብጥብጥ እንደተነሳ የተሰማ ሲሆን ፤ ግቢውም በፌደራል ፖሊሶች እንደተከበበ ይገኛል፡፡ ተማሪዎቹ ከቀን ጀምሮ ምግብ ባለመመገብ ተቃውሟቸውን የጀመሩ ሲሆን ፤ በአሁኑ ሰዓትም ሁሉም ተማሪዎች ወደ ዶርም አንገባም በማለት ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ተፋጠው ይገኛሉ፡፡ በአከባቢው ላይ ያሉ የሌላ ግቢ ተማሪዎችም ብጥብጡ ከአሁን አሁን ወደኛ ጋር ይመጣል በሚል ስጋት በጭንቀት ውስጥ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

በአከባቢው ላይ ብጥብጡ መነሳቱን ተከትሎ ከፍተኛ የኔቶርክ ችግርም በመከሰቱ ተማሪው ያለውን መረጃ እንደፈለገ ለመለዋወጥም እንዳልቻለ አንዳንድ ተማሪዎች ገልፀዋል፡፡ እንደ ምንጮች ዘገባ ከሆነ ተቃውሞው የተነሳው በግቢው ውስጥ የሚማሩ የወተር ኢንጂነሪንግ ተማሪዎች ካነሱት የዲፓርትመንት ስም ይቀየርልን ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሲሆን ፤ በተለያዩ ምክንያቶችም በግቢው ውስጥ የሚማሩ የሁሉም ዲፓርትመንት ተማሪዎች ተቃውሞውን ተቀላቅለውታል፡፡ በአሁን ሰዓት በግቢው ውስጥ የአንደኛ ሲሚስተር የማጠቃለያ ፈተና በመሰጠት ላይ ሲሆን ፤ ሁሉም ተማሪዎችም ጥያቄው መልስ ካላገኘ የነጌውን ፈተኛ እንደማይፈተኑ ገልፀዋል፡፡

No comments: