Friday, November 1, 2013

ስለ ኖርዌይ፤ ስደተኞችና የኢትዮጲያ መንግስት ሰላዮች ማን ይናገር ?

መቀመጫዉን ሮም-ኢጣሊያ ያደረገዉ አፍሪቃዉያን ስደተኞችን የሚረዳዉ አበሻ ኤጀንሲ የተሰኘዉ ግብረሰናይ ድርጅት ኃላፊ ስደተኞችን በመርዳት ስም የሚቀርቡ የኤርትራ መንግስት ሰላዮች መኖራቸዉን አጋለጡ።
የፈረንሳይ የዜና ወኪል አባ ሙሴ ዘርዓይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአስተርጓሚነትና በአግባቢነት ከተሰማሩ አንዳንዶቹ ለፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ መንግስት እንደሚሰሩ መግለጻቸዉን ዘግቧል። እሳቸዉ እንደሚሉትም በአደገኛዉ የባህር ላይ ጉዞ አልፈዉ ነፍሳቸዉ የተረፈ ስደተኞችን ጉዳይ ለፖሊስ ከሚተረጉሙት ጥቂቱ ይህን ተግባር የሚያከናዉኑት ስማቸዉንና አስጊ የሚሉትን መረጃ ለመሰብሰብ ነዉ። በተጨማሪም የኤርትራን መንግስት ለመከላከልም ስደተኞቹ በኤኮኖሚ ችግር ብቻ ከሀገራቸዉ እንደተሰደዱ በማስመሰል የተሳሳተ መረጃ እንደሚሰጡም አባ ሙሴ ይፋ አድርገዋል። በእነዚህ ሰዎች አማካኝነት የሚሰበሰበዉ መረጃም ወደአስመራ መንግስት ተልኮ የስደተኞቹን ቤተሰቦች ንብረት የመዉረስ ወይም በእስራት እንዲቀጡ እንደሚያስደርግም አብራርተዋል። እሳቸዉ እንዳሉትም የሚጠረጥሯቸዉን አስተርጓሚዎች ስም ማንነታቸዉ እንዲጣራ ለሚመለከተዉ ሕጋዊ አካል አስተላልፈዋል። እስካሁን ግን ምላሽ አላገኙም። አብዛኛዉ በዓለም ዓቀፍ የባህር ክልል የሚከሰት በመሆኑ እንዳልተመዘገበ ቢያመለክቱም ከጎርጎሪዮሳዊዉ 2010 አንስቶ እንከአሁን ድረስም ሜዲትራኒያን ባህርን ሲያቋርጡ ወደ2,500 ኤርትራዉያን ማለቃቸዉን አባ ሙሱ ገልጸዋል። ባለፈዉ ላምፔዱዛ ደሴት አቅራቢያ ስደተኞች ላይ አደጋ በደረሰ ወቅት በአካባቢዉ ቢታዩም ርዳታ እንዳላደረጉ የተገለጸ ሁለት ጀልባዎችን ጉዳይ እንዲያጣሩም የጣሊያን ባለስጣናትን ጠይቀዋል።

No comments: