ኢትዮጵያ መንግስት የኖርዌይንና የስዊዲን መንግስታት በዋና ከተሞቻቸው ላይ በልማት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ለማነጋገር በውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ በኩል ያቀረበውን ጥያቄ ሁለቱም አገሮች አልተቀበሉትም። የሁለቱ አገሮች መንግስታት በኢትዮጵያ መንግስት ከቀረቡት የልማት አጀንዳዎች ይልቅ በዋናነት ማንሳት የሚፈልጉተን የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን በመሆኑና የልማት ጉዳዮችን በአምባሳደሮቻቸው በኩል ማሳወቅ እንደሚቻል በማስረገጥ ጥያቄውን አጣጥለውታል።
በቅርቡ ስልጣን የጨበጠው የኖርዌይ የወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ስብስብ መንግስትና የስዊዲን ማዕከላዊ ቀኝ ክንፍ መንግስት እርዳታ የምንሰጠው የዜጎቻቸውን የሰብዓዊ መብትና የፖለቲካ ነፃነት ለሚያከብሩ ታዳጊ አገራት ብቻ ነው የሚል የጠበቀ አቋም መያዛቸው ይታወቃል።
በህዳር ወር 2013 አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂውማን ራይት ዋች የተባለው ድርጅት ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መንግስት አዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ላይ ይፈፀምባቸዋል ያላቸውን ግፎች በ 71 ገፅ ሪፖርት አጋልጧል። በአዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ከሚፈፀሙት የሰብዓዊ መብት ጥቃቶች መካከል ድብደባ፣ በኤሌትክሪክ ማቃጠል፣ ዘቅዝቆ መስቀልና መግረፍ፣ በወንዶች ብልት ላይ በውሃ የተሞላ ጠርሙስ ማሰር፣ ማኮላቨት፣ ተዘቅዝቆ የተሰቀለ ሰውን ውሃ የተሞላ በርሜል ውስጥ መንከር፣ በቀይ አሸዋ ላይ እየገረፉ ማስሮጥ፣ ውስጥ እግር መግረፍ፣ የእግር አውራ ጣት ብቻ መሬት እንዲነካ አርጎ በገመድ መስቀል፣ የተገረፈ አካል ላይ ቀዝቃዛ ውሃ መከለስ፣ ጥርሶችን ማርገፍ ከተጠቀሱት የግፍ ጥቃቶች ጥቂቶቹ ናቸው። እነዚህ ጥቃቶች በሚፈፀሙበት ጊዜ ተጠቂዎቹ ሴቶችም ወንዶችም እርቃናቸው ሆነው ጣውላ ቤት እና ጨለማ ቤት እየተባሉ በሚጠሩት ክፍሎች ውስጥ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሁማን ራይት ዋች ዘግቧዋል። ሁማን ራይት ዋች 32 የቀድሞ እስረኞችን በማነጋገር ባወጣው ሪፖርት ገፅ 9 ላይ ለጋሽ አገሮች ይህን አስቃቂ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ከእርዳታ ፖሊሲያችው ጋር አብረው እንዲያዩት ይማፀናል። በኖርዌይ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይህን ግፍ የሚፈፅመውን የወያኔ መንግስት ይደግፋሉ። ከነዚህ መሃል በከፊል በስደተኛ መኖሪያ ተሰግስገው የራሳቸውን ዜጎች መሰለልን ስራዬ ብለው የሚኖሩ እንዳሉ የኖርዌይ መንግስት ሳይቀር እንደሚያውቀው ግልፅ ነው።
የኢትዮጵያ አንድነት ለዘላለም ይኖራል!!
No comments:
Post a Comment